8 “ምነው ልመናዬ በተመለሰልኝ፤እግዚአብሔር የምመኘውን በሰጠኝ፤
9 እግዚአብሔር አድቅቆ ያጠፋኝ ዘንድ፣ምነው እጁ በተፈታ!
10 ፋታ በማይሰጥ ሕመም ውስጥ እየተደሰትሁ፣ይህ መጽናኛ በሆነልኝ ነበር፤የቅዱሱን ትእዛዝ አልጣስሁምና።
11 “አሁንም ተስፋ አደርግ ዘንድ ብርታቴ፣እታገሥስ ዘንድ አለኝታዬ ምንድን ነው?
12 የድንጋይ ጒልበት አለኝን?ሥጋዬስ ናስ ነውን?
13 ያልተሳካልኝ ሰው ነኝና፣ራሴን ለመርዳት ምን ጒልበት አለኝ?
14 “ለወዳጁ በጎነት የማያሳይ ሰው፣ሁሉን የሚችለውን አምላክ መፍራት ትቶአል።