1 “የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ተጋድሎ አይደለምን?ዘመኑስ እንደ ምንደኛ ዘመን አይደለምን?
2 የምሽትን ጥላ እንደሚመኝ አገልጋይ፣ደመወዙንም እንደሚናፍቅ ምንደኛ፣
3 እንዲሁ ከንቱ ወራት ታደሉኝ፣የጒስቍልና ሌሊቶችም ተወሰኑልኝ።
4 በተኛሁ ጊዜ ‘መቼ ነግቶ እነሣለሁ?’እላለሁ፤ ሌሊቱ ይረዝማል፤ እስኪነጋም እገላበጣለሁ።
5 አካሌ ቈስሎ ትልና ቅርፊት ለብሶአል፤ቈዳዬ አፈክፍኮአል፤ ቍስሌም አመርቅዞአል።