2 “እንዲህ ያለውን ነገር የምትናገረው፣ቃልህም እንደ ብርቱ ነፋስ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?
3 እግዚአብሔር ፍትሕን ያጣምማልን?ሁሉን ቻይ አምላክስ ጽድቅን ያጣምማልን?
4 ልጆችህ በእርሱ ላይ ኀጢአት ሠርተው ከሆነ፣ለኀጢአታቸው ቅጣት አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል።
5 ነገር ግን አንተ ወደ እግዚአብሔር ብትመለከት፣ሁሉን ቻይ አምላክን ብትማፀን፣
6 ንጹሕና ቅን ብትሆን፣ እርሱ ስለ አንተ አሁኑኑ ይነሣል፤ወደ ተገቢውም ስፍራህ ይመልስሃል።
7 ጅማሬህ አነስተኛ ቢመስልም፣ፍጻሜህ እጅግ ታላቅ ይሆናል።
8 “የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፤አባቶቻቸውም የደረሱበትን መርምረህ አግኝ፤