5 ነገር ግን አንተ ወደ እግዚአብሔር ብትመለከት፣ሁሉን ቻይ አምላክን ብትማፀን፣
6 ንጹሕና ቅን ብትሆን፣ እርሱ ስለ አንተ አሁኑኑ ይነሣል፤ወደ ተገቢውም ስፍራህ ይመልስሃል።
7 ጅማሬህ አነስተኛ ቢመስልም፣ፍጻሜህ እጅግ ታላቅ ይሆናል።
8 “የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፤አባቶቻቸውም የደረሱበትን መርምረህ አግኝ፤
9 እኛ ትናንት ስለ ተወለድን አንዳች አናውቅምና፤ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው።
10 እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፣ከልቦናቸውም ቃልን የሚያወጡ አይደሉምን?
11 ደንገል ረግረግ በሌለበት ስፍራ ይበቅላልን?ቄጠማስ ውሃ በሌለበት ይለመልማልን?