1 ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፤
2 “በእርግጥ ነገሩ እንዲህ እንደሆነ ዐውቃለሁ፤ነገር ግን ሥጋ ለባሽ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ጻድቅ ሊሆን ይችላል?
3 ሰው ከእርሱ ጋር ለመከራከር ቢፈልግ፤ከሺህ ጥያቄ እንዱን እንኳ መመለስ አይችልም።
4 ጥበቡ ጥልቅ፣ ኀይሉም ታላቅ ነውና፤እርሱን ተቃውሞ ያለ አንዳች ጒዳት የሄደ ማን ነው?
5 ሳያውቁት፣ ተራሮችን ይነቅላቸዋል፤በቍጣውም ይገለብጣቸዋል።
6 ምድርን ከስፍራዋ ያናውጣታል፤ምሰሶዎቿንም ያንቀጠቅጣል።