18 ምሬትን አጠገበኝ እንጂ፣ለመተንፈስ እንኳ ፋታ አልሰጠኝም።
19 የኀይል ነገር ከተነሣ፣ እርሱ ኀያል ነው!የፍትሕም ነገር ከተነሣ፣ መጥሪያ ሊሰጠው የሚችል ማን ነው?
20 ንጹሕ ብሆን እንኳ፣ አንደበቴ ይፈርድብኛል፣እንከን የለሽ እንኳ ብሆን፣ በደለኛ ያደርገኛል።
21 “ያለ ነቀፋ ብሆንም እንኳ፣ስለ ራሴ ግድ የለኝም፤የገዛ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።
22 ሁሉም አንድ ነው፤‘እርሱ ጻድቁንና ኀጥኡን ያጠፋል’ የምለውም ለዚህ ነው።
23 መዓት ወርዶ ድንገት ሰው ሲጨርስ፣በንጹሓን መከራ ይሣለቃል።
24 ምድር በክፉዎች እጅ ስትወድቅ፣እርሱ የፈራጆቿን ዐይን ይሸፍናል፤ታዲያ፣ ይህን ያደረገው እርሱ ካልሆነ ማን ሊሆን ይችላል?