24 ምድር በክፉዎች እጅ ስትወድቅ፣እርሱ የፈራጆቿን ዐይን ይሸፍናል፤ታዲያ፣ ይህን ያደረገው እርሱ ካልሆነ ማን ሊሆን ይችላል?
25 “ዘመኔ ከሚሮጥ ሰው ይልቅ ይፈጥናል፣አንዳችም ደስታ ሳያይ ያልፋል።
26 ከደንገል እንደ ተሠራ ታንኳ፣ለመንጠቅ ቍልቍል እንደሚበር ንስር ይፈጥናል።
27 ‘ማጒረምረሜን እረሳለሁ፤ገጽታዬን ቀይሬ ፈገግ እላለሁ’ ብል፣
28 ንጹሕ አድርገህ እንደማትቈጥረኝ ስለማውቅ፣መከራዬን ሁሉ እፈራለሁ።
29 በደለኛ መሆኔ ካልቀረ፣ለምን በከንቱ እለፋለሁ?
30 ሰውነቴን በሳሙና ብታጠብ፣እጄንም በልዩ መታጠቢያ ባነጻ፣