4 ጥበቡ ጥልቅ፣ ኀይሉም ታላቅ ነውና፤እርሱን ተቃውሞ ያለ አንዳች ጒዳት የሄደ ማን ነው?
5 ሳያውቁት፣ ተራሮችን ይነቅላቸዋል፤በቍጣውም ይገለብጣቸዋል።
6 ምድርን ከስፍራዋ ያናውጣታል፤ምሰሶዎቿንም ያንቀጠቅጣል።
7 ፀሓይን ያዛታል፤ አትወጣምም፤ከዋክብትንም በማኅተም ያሽጋል።
8 እርሱ ብቻውን ሰማያትን ዘርግቶአል፤በባሕርም ማዕበል ላይ ይራመዳል።
9 እርሱ የድብና የኦሪዮን፣የፕልያዲስና የደቡብ ከዋክብት ፈጣሪ ነው፤
10 የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮችን፣የማይቈጠሩ ታምራትንም ያደርጋል።