8 እርሱ ብቻውን ሰማያትን ዘርግቶአል፤በባሕርም ማዕበል ላይ ይራመዳል።
9 እርሱ የድብና የኦሪዮን፣የፕልያዲስና የደቡብ ከዋክብት ፈጣሪ ነው፤
10 የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮችን፣የማይቈጠሩ ታምራትንም ያደርጋል።
11 እነሆ! በአጠገቤ ሲያልፍ አላየውም፤በጐኔም ሲሄድ፣ ልገነዘበው አልችልም።
12 ቢነጥቅ፣ ማን ይከለክለዋል?‘ምን መሥራትህ ነው?’ የሚለውስ፣ ማን ነው?
13 እግዚአብሔር ቍጣውን አይመልስም፤ረዓብን የሚረዱ እንኳ ይሰግዱለታል።
14 “ታዲያ፣ ከእርሱ ጋር እሟገት ዘንድ፣ልከራከረውም ቃላት እመርጥ ዘንድ፣ እንዴት እችላለሁ?