3 ሰኰናው የተሰነጠቀውን የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ መብላት ትችላላችሁ።
4 “ ‘የሚያመሰኩ ሆነው ሰኰናቸው ያልተሰነጠቀ ወይም ሰኰናቸው የተሰነጠቀ ሆኖ የማያመሰኩትን አትብሉ፤ ግመል ያመሰኳል፤ ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ ግን በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።
5 ሽኮኮ ያመስኳል፤ ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ ግን በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።
6 ጥንቸል ያመሰኳል፤ ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ ግን በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።
7 ዐሳማ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።
8 የእነዚህን እንስሳት ሥጋ አትብሉ፤ ጥንባቸውንም አትንኩ፤ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ይሁኑ።
9 “ ‘በባሕሮችና በወንዞች ውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ፍጡሮች ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን መብላት ትችላላችሁ፤