ዘሌዋውያን 13:30-36 NASV

30 ካህኑ ቊስሉን ይመርምር፤ ከቈዳው በታች ዘልቆ ከገባ፣ በውስጡም ያለው ጠጒር ቢጫና ቀጭን ከሆነ ያ ሰው ርኩስ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ፤ የሚያሳክክ የራስ ወይም የአገጭ ተላላፊ በሽታ ነው።

31 ካህኑ እንዲህ ዐይነቱን ቊስል በሚመረምርበት ጊዜ፣ ከቈዳው በታች ዘልቆ ካልገባና በውስጡም ጥቊር ጠጒር ከሌለ፣ ካህኑ ሰውየውን ሰባት ቀን ያግልለው።

32 ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቊስሉን ይመርምር፤ የሚያሳክከው ቦታ ያልሰፋ፣ ቢጫ ጠጒር የሌለውና ከቈዳው በታች ዘልቆ ያልገባ ከሆነ፣

33 ከቈሰለው ቦታ በስተቀር ጠጒሩን ይላጭ፤ ካህኑ ሰባት ተጨማሪ ቀን ሰውየውን ያግልል።

34 ካህኑ በሰባተኛው ቀን የሚያሳክከውን የሰውየውን ቊስል ይመርምር፤ በቈዳው ላይ ካልሰፋና ከቈዳው በታች ዘልቆ ካልገባ ካህኑ ያ ሰው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ፤ ልብሱን አጥቦ ንጹሕ ይሁን።

35 ንጹሕ መሆኑ ከተገለጠ በኋላ ግን የሚያሳክከው ቊስል ተስፋፍቶ ቢገኝ፣

36 ካህኑ ይመርምረው፤ ቊስሉ በቈዳው ላይ ከሰፋ፣ ካህኑ የጠጒሩን ቢጫ መሆን አለመሆን ማየት አያሻውም፤ ሰውየው ርኩስ ነው።