37 ነገር ግን ቊስሉ በካህኑ አመለካከት ለውጥ ያላሳየ ከሆነና በውስጡ ጥቊር ጠጒር ካበቀለ ቊስሉ ድኖአል፤ ሰውየው ነጽቶአል፤ ካህኑም ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ።
38 “በወንድ ወይም በሴት ቈዳ ላይ ቋቍቻ ቢወጣ፣
39 ካህኑ ይመርምራቸው፤ ቋቍቻው ዳለቻ ከሆነ በቈዳ ላይ የወጣ ጒዳት የማያስከትል ችፍታ ነው፤ ሰውየውም ንጹሕ ነው።
40 “አንድ ሰው የራሱ ጠጒር ከዐናቱ አልቆ መላጣ ቢሆን ንጹሕ ነው።
41 ጠጒሩ ከፊት ለፊት ተመልጦ ራሰ በራ ቢሆንም ንጹሕ ነው።
42 ነገር ግን በመላጣው ወይም በበራው ላይ ነጣ ያለ ቀይ ቊስል ቢወጣበት፣ ያ ከመላጣው ወይም ከበራው የወጣ ተላላፊ በሽታ ነው።
43 ካህኑ ይመርምረው፤ በመላጣው ወይም በበራው ላይ ያበጠው ተላላፊ የቈዳ በሽታ የሚመስል ነጣ ያለ ቊስል ከሆነ፣