16 “ ‘ከወንድምህ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ ወንድምህን ያዋርዳል።
17 “ ‘ከእናቲቱና ከሴት ልጇ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ከወንድ ልጇ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እነርሱ የሥጋ ዘመዶቿ ናቸው፤ ይህም ጸያፍ ነው።
18 “ ‘ሚስትህ በሕይወት እያለች እኅቷን ጣውንት አድርገህ አታግባት፤ ከእርሷም ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም።
19 “ ‘በወር አበባዋ ርኵሰት ጊዜ ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ወደ ሴት አትቅረብ።
20 “ ‘ከባልንጀራህ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም፣ ራስህን በእርሷ አታርክስ።
21 “ ‘ከልጆችህ ማንኛውንም ለሞሎክ እንዲሠዋ አሳልፈህ አትስጥ፤ የአምላክህንም (ኤሎሂም) ስም አታርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።
22 “ ‘ከሴት ጋር እንደሚደረገው ሁሉ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ይህ አስጸያፊ ነው።