13 “ ‘ካህኑ የሚያገባት ሴት ድንግል ትሁን።
14 ባል የሞተባትን፣ የተፋታችውን ወይም በዝሙት ዐዳሪነት የረከሰችውን ሴት አያግባ፤ ነገር ግን ከወገኖቹ መካከል ድንግሊቱን ያግባ።
15 በወገኖቹ መካከል ዘሩን አያርክስ። እርሱን የምቀድሰው እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”
16 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
17 “አሮንን እንዲህ በለው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ከዘርህ እንከን ያለበት ማንኛውም ሰው የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ይሠዋ ዘንድ አይቅረብ።
18 ዕውር ወይም አንካሳ፣ የፊቱ ገጽታ ወይም የሰውነቱ ቅርጽ የተበላሸ ማንኛውም የአካል ጒድለት ያለበት ሰው አይቅረብ።
19 እንዲሁም እግሩ ወይም እጁ ሽባ የሆነ፣