16 የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም የሚሳደብ ማንኛውም ሰው ይገደል፤ ማኅበሩ ሁሉ ይውገሩት፤ መጻተኛም ሆነ የአገር ተወላጅ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም ከሰደበ ይገደል።
17 “ ‘ሰውን ደብድቦ የገደለ ይገደል።
18 የሌላውን ሰው እንስሳ ደብድቦ የገደለ ማንኛውም ሰው ያንኑ ዐይነት እንስሳ ይተካለት።
19 ማንኛውም ሰው በባልንጀራው ላይ ጒዳት ቢያደርስ የዚያው ዐይነት ጒዳት ይፈጸምበት፤
20 ይኸውም በስብራት ፈንታ ስብራት፣ በዐይን ፈንታ ዐይን፣ በጥርስ ፈንታ ጥርስ ማለት ነው። በሌላው ሰው ላይ ያደረሰው ጒዳት በእርሱም ላይ ይድረስበት፤
21 እንስሳ የገደለ ማንኛውም ሰው በገደለው ፈንታ ይተካ፤ ሰው የገደለ ግን ይገደል።
22 ለመጻተኛው ሆነ ለአገር ተወላጅ አንድ ዐይነት ሕግ ይኑራችሁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።’ ”