ዘሌዋውያን 3:1-7 NASV

1 “ ‘ማንኛውም ሰው የሚያቀርበው ቊርባን ከላሞች መንጋ የሚቀርብ የኅብረት መሥዋዕት ከሆነ፣ እንከን የሌለበትን ተባዕት ወይም እንስት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያቅርብ።

2 በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ይረደው፤ ካህናቱም የአሮን ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት።

3 ከኅብረት መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ ቊርባን አድርጎ ያምጣ፤ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ በሆድ ዕቃው ላይ ያለውን ሥብ ሁሉ፣

4 ሁለቱን ኵላሊቶች፣ በኵላሊቶቹ ላይና በጐድኑ አጠገብ ያለውን ሥብ እንዲሁም የጒበቱን መሸፈኛ ከኵላሊቶቹ ጋር አንድ ላይ አውጥቶ ያቅርብ።

5 የአሮንም ልጆች በመሠዊያው በሚነደው ዕንጨት ላይ ባለው በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አድርገው ያቃጥሉት፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ይሆናል።

6 “ ‘ከበግ ወይም ከፍየሉ መንጋ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የኅብረት መሥዋዕት የሚያቀርብ ከሆነ፣ እንከን የሌለበትን ተባዕት ወይም እንስት ያቅርብ።

7 መሥዋዕቱ የበግ ጠቦት ከሆነም፣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያምጣው፤