2 “የወንዶቹን ስም አንድ በአንድ በመዘርዘር መላውን የእስራኤል ማኅበረሰብ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው ቍጠሯቸው።
3 በመላው እስራኤል ያሉትን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያም በላይ ሆኖ ለውጊያ ብቁ የሆኑትን ወንዶች ሁሉ አንተና አሮን በየምድባቸው ቍጠሯቸው።
4 ከየነገዱ የአባቶች ቤት ተጠሪ የሆነ አንድ ሰው ከእናንተ ጋር ይሁን።
5 የሚረዷችሁም ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፦“ከሮቤል የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር፤
6 ከስምዖን የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል፤
7 ከይሁዳ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፤
8 ከይሳኮር የሶገር ልጅ ናትናኤል፤