ዘኁልቍ 10:27-33 NASV

27 እንዲሁም የንፍታሌም ነገድ ሰራዊት አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ነበር።

28 እንግዲህ የእስራኤል ሰራዊት የጒዞ አሰላለፍ ሥርዐት ይህ ነበር።

29 በዚህ ጊዜ ሙሴ የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፣ “እነሆ፤ እግዚአብሔር፣ (ያህዌ) ‘እሰጣችኋለሁ’ ወዳለን ምድር ጒዞ ጀምረናል፤ በመልካም ሁኔታ ስለምናኖርህ ከእኛ ጋር ሂድ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ለእስራኤል በጎ ነገር ለማድረግ ቃል ገብቶአልና አለው።”

30 እርሱም መልሶ፣ “ይህስ አይሆንም፤ አልሄድም፤ ወደ አገሬና ወደ ወገኖቼ ተመልሼ እሄዳለሁ” አለው።

31 ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “እባክህ አትለየን፤ በምድር በዳ ውስጥ የት መስፈር እንደሚገባን አንተ ታውቃለህ፤ ዐይናችንም ትሆናለህ።

32 ከእኛ ጋር ብትሄድ እግዚአብሔር (ያህዌ) ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛም እናደርግልሃለን።”

33 ስለዚህ ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ተራራ ተነሥተው የሦስት ቀን መንገድ ተጓዙ፤ የእግዚአብሔር (ያህዌ) ቃል ኪዳን ታቦትም በእነዚያ ሦስት ቀናት ውስጥ የሚያርፉበትን ቦታ በመፈለግ ፊት ፊታቸው ይሄድ ነበር።