2 “ለእስራኤላውያን የምሰጠውን የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ጥቂት ሰዎች ላክ፤ ከእያንዳንዱም የአባቶች ነገድ አለቃ ይላክ።”
3 ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ እነዚህን ላካቸው፤ ሁሉም የእስራኤላውያን አለቆች ነበሩ፤
4 ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፤ከሮቤል ነገድ፣ የዘኩር ልጅ ሳሙኤል፤
5 ከስምዖን ነገድ፣ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ፤
6 ከይሁዳ ነገድ፣ የዩፎኒ ልጅ ካሌብ፤
7 ከይሳኮር ነገድ፣ የዮሴፍ ልጅ ይግአል፤
8 ከኤፍሬም ነገድ፣ የነዌ ልጅ አውሴ፤