10 “በደቡብ በኩል የሮቤል ምድብ ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ይሆናል፤ የሮቤል ሕዝብ አለቃ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር ሲሆን፣
11 የሰራዊቱም ብዛት አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነው።
12 “ከእነዚህ ቀጥሎ የስምዖን ነገድ ይሰፍራል፤ የስምዖን ሕዝብ አለቃ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል ሲሆን፣
13 የሰራዊቱም ብዛት አምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነው።
14 “ከዚያም የጋድ ነገድ ይቀጥላል፤ የጋድ ሕዝብ አለቃ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ሲሆን፣
15 የሰራዊቱም ብዛት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አምሳ ነው።
16 በየሰራዊታቸው ሆነው ከሮቤል ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ አንድ መቶ አምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ አምሳ ናቸው፤ እነዚህ ቀጥለው ይመጣሉ።