3 “በምሥራቅ በኩል በፀሓይ መውጫ የይሁዳ ምድብ በየሰራዊቱና በዐርማቸው ሥር ይስፈር፤ የይሁዳ ሕዝብ አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው፤
4 የሰራዊቱም ብዛት ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነው።
5 “ከእነዚህ ቀጥሎ የይሳኮር ነገድ ይሰፍራል፤ የይሳኮር ሕዝብ አለቃ የሶገር ልጅ ናትናኤል ሲሆን፣
6 የሰራዊቱም ብዛት አምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነው።
7 “ከዚያም የዛብሎን ነገድ ይቀጥላል፤ የዛብሎን ሕዝብ አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣
8 የሰራዊቱም ብዛት አምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነው።
9 በየሰራዊታቸው ሆነው ከአይሁድ ምድብ የተመዘገቡ አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ናቸው፤ እነዚህ አስቀድመው ይወጣሉ።