1 ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ወደ ሞዓብ ሜዳ ተጒዘው ከዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ከኢያሪኮ ማዶ ሰፈሩ።
2 በዚህ ጊዜ የሴፎር ልጅ ባላቅ፣ እስራኤል በአሞራውያን ላይ ያደረገውን ሁሉ አየ፤
3 ሞዓብም ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ተሸበረ፤ በእርግጥም ሞዓብ በእስራኤላውያን ምክንያት በፍርሀት ተውጦ ነበር።
4 ሞዓባውያንም የምድያምን ሽማግሌዎች፣ “በሬ የመስክ ሣር ጠራርጎ እንደሚበላ ሁሉ፣ ይህም ሰራዊት በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ ነው” አሏቸው።ስለዚህ በዚያን ጊዜ የሞዓብ ንጉሥ የነበረው የሴፎር ልጅ ባላቅ፣