16 እግዚአብሔር (ያህዌ) በለዓምን ተገናኘው፤ በአፉም መልእክት አስቀምጦ፣ “ወደ ባላቅ ተመለስና ይህን መልእክት ንገረው” አለው።
17 እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅን ከመላው የሞዓብ አለቆች ጋር በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አገኘው፤ ባላቅም፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ምን አለ?” ሲል ጠየቀው።
18 ከዚያም ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤“ባላቅ ሆይ ተነሣ፤ አድምጠኝ፤የሴፎር ልጅ ሆይ ስማኝ፤
19 ይዋሽ ዘንድ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰው አይደለም፤ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም፤ተናግሮ አያደርገውምን?ተስፋ ሰጥቶስ አይፈጽመውምን?
20 እባርክ ዘንድ ትእዛዝ ተቀብያለሁ፤እርሱ ባርኳል፤ እኔም ልለውጠው አልችልም።
21 “በያዕቆብ መጥፎ ነገር አልተገኘም፤በእስራኤልም ጒስቍልና አልታየም፤ እግዚአብሔር አምላኩ (ያህዌ ኤሎሂም) ከእርሱ ጋር ነው፣የንጉሡም እልልታ በመካከላቸው ነው።
22 እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ከግብፅ አወጣቸው፤ብርታታቸውም እንደ ጎሽ ብርታት ነው።