1 ከመቅሠፍቱ በኋላ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፤
2 “ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን፣ በእስራኤልም ጦር ሰራዊት ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ሁሉ ከመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ከየቤተ ሰቡ ቊጠሩ።”
3 ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤
4 “እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።”ከግብፅ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤
5 የእስራኤል የበኵር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤በሄኖኀ በኩል፣ የሄኖኀውያን ጐሣ፤በፈለስ በኩል፣ የፈሉሳውያን ጐሣ፤
6 በአስሮን በኩል፣ የአስሮናውያን ጐሣ፤በከርሚ በኩል፣ የከርማውያን ጐሣ፤
7 እነዚህ የሮቤል ጐሣዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።