25 እነዚህ የይሳኮር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሥልሳ አራት ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ።
26 የዛብሎን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በሴሬድ በኩል፣ የሴሬዳውያን ጐሣ፤በኤሎን በኩል፣ የኤሎናውያን ጐሣ፣በያሕልኤል በኩል፣ የያሕልኤላውያን ጐሣ፤
27 እነዚህ የዛብሎን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሥልሳ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።
28 የዮሴፍ ዘሮች በምናሴና በኤፍሬም በኩል ያሉት በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
29 የምናሴ ዘሮች፤በማኪር በኩል፣ የማኪራውያን ጐሣ፤ ማኪርም የገለዓድ አባት ነው፤በገለዓድ በኩል፣ የገለዓዳውያን ጐሣ፤
30 የገለዓድ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤በኢዔዝር በኩል፣ የኢዓዝራውያን ጐሣ፣በኬሌግ በኩል፣ የኬሌጋውያን ጐሣ፣
31 በአሥሪኤል በኩል፣ የአሥሪኤላውያን ጐሣ፣በሴኬም በኩል፣ የሴኬማውያን ጐሣ፣