28 የዮሴፍ ዘሮች በምናሴና በኤፍሬም በኩል ያሉት በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
29 የምናሴ ዘሮች፤በማኪር በኩል፣ የማኪራውያን ጐሣ፤ ማኪርም የገለዓድ አባት ነው፤በገለዓድ በኩል፣ የገለዓዳውያን ጐሣ፤
30 የገለዓድ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤በኢዔዝር በኩል፣ የኢዓዝራውያን ጐሣ፣በኬሌግ በኩል፣ የኬሌጋውያን ጐሣ፣
31 በአሥሪኤል በኩል፣ የአሥሪኤላውያን ጐሣ፣በሴኬም በኩል፣ የሴኬማውያን ጐሣ፣
32 በሸሚዳ በኩል፣ የሸሚዳውያን ጐሣ፣በኦፌር በኩል፣ የኦፌራውያን ጐሣ፣
33 የኦፌር ልጅ ሰለጰዓድ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላሉ።
34 እነዚህ የምናሴ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ።