3 ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤
4 “እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።”ከግብፅ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤
5 የእስራኤል የበኵር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤በሄኖኀ በኩል፣ የሄኖኀውያን ጐሣ፤በፈለስ በኩል፣ የፈሉሳውያን ጐሣ፤
6 በአስሮን በኩል፣ የአስሮናውያን ጐሣ፤በከርሚ በኩል፣ የከርማውያን ጐሣ፤
7 እነዚህ የሮቤል ጐሣዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።
8 የፈሉስ ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣
9 የኤልያብ ልጆች ደግሞ፣ ነሙኤል ዳታንና አቤሮን ነበሩ። እነዚሁ ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁ የማኅበሩ ሹማምት ሲሆኑ፣ ቆሬና ተከታዮቹ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ላይ ባመፁ ጊዜ እነርሱም በነገሩ ነበሩበት።