52 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
53 “ምድሪቱ በስማቸው ቍጥር ልክ ተደልድላ በርስትነት ለእነርሱ ትሰጥ።
54 በርከት ያለ ቊጥር ላለው ጐሣ ሰፋ ያለውን ርስት፣ አነስ ያለ ቊጥር ላለው ጐሣ ደግሞ አነስ ያለውን ስጥ፤ ርስቱንም እያንዳንዱ በዝርዝሩ ላይ በተመለከተው ቊጥር መሠረት ይረከባል።
55 የመሬት ድል ድሉም በዕጣ ይሁን፤ እያንዳንዱ የሚወርሰውም በየነገድ አባቶቹ ስም ይሆናል።
56 እያንዳንዱም ርስት በትል ልቆቹና በትንንሾቹ ነገዶች መካከል በዕጣ ይደለደላል።
57 በየጐሣቸው የተቈጠሩት ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤በጌድሶን በኩል፣ የጌድሶናውያን ጐሣ፣በቀዓት በኩል፣ የቀዓታውያን ጐሣ፣በሜራሪ በኩል፣ የሜራራውያን ጐሣ፤
58 እነዚህም ደግሞ የሌዊ ጐሣዎች ነበሩ፤የሊብናውያን ጐሣ፣የኬብሮናውያን ጐሣ፣የሞሖላውያን ጐሣ፣የሙሳውያን ጐሣ፣የቆሬያውያን ጐሣ።ቀዓት የእንበረም ቅድመ አያት ነበር፤