ዘኁልቍ 29:4-10 NASV

4 ከእያንዳንዱም ሰባት የበግ ጠቦት ጋር በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት አዘጋጁ።

5 ማስተስረያ እንዲሆናችሁም አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት በማድረግ በተጨማሪ አቅርቡ።

6 እነዚህ እንግዲህ በተደነገገው መሠረት ከእህል ቍርባናቸውና ከመጠጥ ቍርባናቸው ጋር በየዕለቱና በየወሩ ከሚቀርቡት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሌላ ተጨማሪ ሆነው፣ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ሽታቸው ደስ የሚያሰኝ በእሳት የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ናቸው።

7 “ ‘በዚሁ በሰባተኛው ወር በዐሥረኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ ራሳችሁን አዋርዱ፤ ሥራም አትሥሩ።

8 ሁሉም እንከን የሌለባቸው አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች፣ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ።

9 ከወይፈኑ ጋር ለእህል ቍርባን የሚሆን የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከአውራ በጉ ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ በዘይት የተለወሰ ዱቄት አቅርቡ፤

10 ከሰባቱ የበግ ጠቦቶችም ከእያንዳንዳቸው ጋር በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት አዘጋጁ።