ዘኁልቍ
ምዕራፎች 3:15-21
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
15“ሌዋውያንን በየቤታቸውና በየጐሣቸው ቍጠር፤ የምትቈጥረውም አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ ነው” አለው።
16ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ቃል በታዘዘው መሠረት እነዚህን ቈጠራቸው።
17የሌዊ ልጆች ስምጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ነው።
18የጌድሶን ልጆች ጐሣ ስምሎቢኒና ሰሜኢ ነው።
19የቀዓት ጐሣዎች፤እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል።
20የሜራሪ ጐሣዎች፤ሞሖሊና ሙሲ።እንግዲህ የሌዋውያን ጐሣዎች በየቤተ ሰባቸው ሲቈጠሩ እነዚህ ናቸው።
21የሎቤናና የሰሜአ ጐሣዎች ከጌርሶን ወገን ናቸው፤ እነዚህ የጌርሶን ጐሣዎች ነበሩ።