5 እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
6 “የሌዊን ነገድ አምጥተህ ካህኑን አሮንን በአገልግሎቱ እንዲረዱት ከፊቱ አቁማቸው፤
7 በመገናኛው ድንኳን የማደሪያውን አገልግሎት በመፈጸም ለእርሱና ለማኅበረ ሰቡ ሁሉ የሚያስፈልጉትን ተግባሮች ያከናውኑ፤
8 የማደሪያውን ሥራ በመሥራትና የእስራኤላውያንን ግዴታ በመወጣት የመገናኛውን ድንኳን ሁሉ ይጠብቁ።
9 ሌዋውያኑን ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ፤ እነርሱም ከእስራኤላውያን ተለይተው ለእርሱ ፈጽመው የተሰጡ ናቸው።
10 አሮንንና ልጆቹን ሹማቸው፤ እነርሱም ክህነታቸውን ይጠብቁ፤ ሌላ ሰው ማደሪያውን ቢቀርብ ግን ይገደል።”
11 እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤