32 ወታደሮቹ ማርከው ከወሰዱለት ምርኮ ውስጥ የቀረው ይህ ነበር፤ ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ በግ፣
33 ሰባ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብት፣
34 ሥልሳ አንድ ሺህ አህያ
35 ወንድ ያላወቁ ሠላሳ ሁለት ሺህ ሴቶች።
36 በጦርነቱ ላይ የነበሩት ወታደሮች እኩሌታ ድርሻ ይህ ነበር፤ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ በግ፤
37 ከነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠ ግብር ስድስት መቶ ሰባ አምስት ነበር።
38 ሠላሳ ስድስት ሺህ የቀንድ ከብት፣ ከነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠው ግብር ሰባ ሁለት ነበር።