ዘኁልቍ
ምዕራፎች 33:47-53
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
47ከዓልሞንዲብላታይም ተነሥተው በናባው አጠገብ በሚገኙት በዓብሪም ተራራዎች ላይ ሰፈሩ።
48ከዓብሪም ተራራዎች ተነሥተው ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ላይ ሰፈሩ።
49እዚያም በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ከቤት የሺሞት እስከ አቤልስጢም ባለው ስፍራ ሰፈሩ።
50ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
51“እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ወደ ከነዓን ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገሩ፣
52የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አሳዳችሁ አስወጧቸው፤ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንና ቀልጠው የተሠሩ ጣዖቶቻቸውን በሙሉ አጥፉ፤ እንዲሁም በኰረብታ ላይ የተሠሩትን መስገጃዎቻቸውን ሁሉ አፈራርሱ።
53ምድሪቱን ርስት አድርጌ ሰጥቻችኋለሁና ውረሷት፤ ኑሩባትም።