ዘኁልቍ 35:4-10 NASV

4 “በየከተሞቹ ዙሪያ ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸውም የግጦሽ መሬት ከከተማው ቅጥር አንድ ሺህ ክንድ ይዘረጋል።

5 ከዚያም ከተማውን መካከል በማድረግ ወደ ምሥራቅ ሁለት ሺህ ክንድ፣ ወደ ደቡብ ሁለት ሺህ ክንድ፣ ወደ ምዕራብ ሁለት ሺህ ክንድ፣ ወደ ሰሜን ሁለት ሺህ ክንድ ከከተማው ውጭ ለካ፤ እነዚህንም ቦታዎች ለከተሞቹ የግጦሽ መሬት ያደርጓቸዋል።

6 “ለሌዋውያኑ ከምትሰጧቸው ከተሞች ስድስቱ፣ ሰው የገደለ ሸሽቶ የሚጠጋባቸው መማጸኛ ከተሞች ይሆናሉ፤ በተጨማሪም አርባ ሁለት ከተሞች ስጧቸው፤

7 የግጦሽ መሬቶቻቸውን ጨምሮ በጠቅላላው አርባ ስምንት ከተሞች ለሌዋውያኑ ስጧቸው።

8 እስራኤላውያን ከወረሷት ምድር ላይ ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸው ከተሞች እያንዳንዱ ነገድ እንዳለው ድርሻ መጠን ይሆናል። ብዙ ካለው ነገድ ላይ ብዙ ከተሞች እንዲሁም ጥቂት ካለው ነገድ ላይ ጥቂት ከተሞችን ውሰዱ።”

9 ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

10 “እስራኤላውያንን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ወደ ከነዓን ለመግባት ዮርዳኖስን በምትሻገሩበት ጊዜ፣