4 እስራኤላውያን ይህንኑ አደረጉ፤ ሰዎቹንም ከሰፈር አስወጧቸው፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘውም መሠረት ፈጸሙ።
5 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
6 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘ወንድም ሆነ ሴት በማናቸውም ረገድ ሌላውን ቢበድልና ከዚህም የተነሣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ዘንድ ያለውን ታማኝነት ቢያጐድል ያ ሰው በደለኛ ነው
7 በሠራው ኀጢአት ይናዘዝ፤ ሰለበደሉም ሙሉ ካሳ ይክፈል፤ የተመደበበትም ካሳ ላይ አንድ አምስተኛ በመጨመር በደል ላደረሰበት ሰው ይስጥ፤
8 ነገር ግን ይህ ሰው ካሳውን የሚቀበልለት ዘመድ ከሌለው ካሳው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ስለሚሆን ማስተስረያ እንዲሆነው ከሚያቀርበው አውራ በግ ጋር ለካህኑ ይስጥ።
9 እስራኤላውያን የሚያመጧቸው የተቀደሱ ስጦታዎች ሁሉ ለተቀባዩ ካህን ይሆናሉ፤
10 የእያንዳንዱ ሰው የተቀደሰ ስጦታ ለካህኑ ይሆናል፤ ለካህኑ የሚሰጠውም ሁሉ የራሱ ይሆናል።’ ”