4 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
5 “በመገናኛውም ድንኳን ለአገልግሎት እንዲውሉ እነዚህን ከእነርሱ ተቀበል፤ ለእያንዳንዳቸውም ለአገልግሎታቸው በሚያሰፈልጋቸው መጠን ለሌዋውያኑ ስጣቸው።”
6 ስለዚህ ሙሴ ሠረገሎቹንና በሬዎቹን ወስዶ ለሌዋውያኑ ሰጣቸው፤
7 ለጌድሶናውያን ለአገልግሎታቸው በሚያስፈልጋቸው መጠን ሁለት ሠረገሎችና አራት በሬዎች ሰጠ።
8 ለሜራሪያውያንም ለአገልግሎታቸው በሚያስፈልጋቸው መጠን አራት ሠረገሎችና ስምንት በሬዎች ሰጠ። እንግዲህ እነዚህ ሁሉ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር ኀላፊነት የሚመሩ ነበሩ።
9 በኀላፊነት የተሰጧቸውን ንዋያተ ቅዱሳት በትከሻቸው መሸከም ስለነበረባቸው፣ ሙሴ ለቀዓታውያን ምንም አልሰጣቸውም።
10 መሠዊያው በተቀባበት ቀን አለቆች የመሠዊያውን መቀደስ ምክንያት በማድረግ ስጦታዎችን አመጡ፤ በመሠዊያውም ፊት አቀረቡ።