19 እነርሱም፣ “የዕብራውያን ሴቶች እንደ ግብፃውያን ሴቶች አይደሉም፤ ብርቱዎች ስለሆኑ አዋላጆች ከመድረሳቸው በፊት ይወልዳሉ” ሲሉ ለፈርዖን መለሱለት።
20 ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ለአዋላጆቹ መልካም ሆነላቸው፤ ሕዝቡም በቍጥር እየበዛና እያየለ ሄደ።
21 አዋላጆቹም እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) በመፍራታቸው ቤተ ሰብ ሰጣቸው።
22 ፈርዖንም፣ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ አባይ ወንዝ ውስጥ ጣሉት፤ ሴት ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት ትኑር” ሲል ሕዝቡን አዘዘ።