2 ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ድነቴም ሆነልኝ፤እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤የአባቴ አምላክ (ኤሎሂም) ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
3 ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ተዋጊ ነው፤ስሙም እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው።
4 የፈርዖንን ሠረገሎችና ሰራዊት፣ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ምርጥ የሆኑት የፈርዖን ሹማምት፣ቀይ ባሕር ውስጥ ሰጠሙ።
5 ቀላያትንም ለበሱ፤እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ወረዱ።
6 “አቤቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ቀኝ እጅህ በግርማ ከበረ፤አቤቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ቀኝ እጅህ ጠላትን አደቀቀ።
7 በግርማህ ታላቅነት፣የተቃወሙህን ጣልኻቸው፤ቍጣህን ሰደድህ፤እንደ ገለባም በላቸው።
8 በአፍንጫህ እስትንፋስ፣ውሆች ተቈለሉ፤ፈሳሾችም እንደ ግድግዳ ቆሙ፤የጥልቁ ውሃ ባሕሩ ውስጥ ረጋ።