ሉቃስ 13:22-28 NASV

22 ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እያመራ ሳለ፣ በሚያልፍባቸው ከተሞችና መንደሮች እያስተማረ ያልፍ ነበር።

23 አንድ ሰውም ቀርቦ፣ “ጌታ ሆይ፤ የሚድኑት ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸውን?” አለው።እርሱም እንዲህ አላቸው፤

24 “በጠባቧ በር ለመግባት ተጣጣሩ፤ እላችኋለሁ፤ ብዙዎች ለመግባት ይፈልጋሉ ነገር ግን አይሆንላቸውም፤

25 የቤቱ ባለቤት ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ በውጭ ቆማችሁ፣ ጌታ ሆይ፤ ክፈትልን እያላችሁ በሩን ማንኳኳት ትጀምራላችሁ። “እርሱ ግን፣ ‘ማን እንደሆናችሁና ከየት እንደመጣችሁ አላውቅም’ ብሎ ይመልስላችኋል።

26 “እናንተም፣ ከአንተ ጋር አብረን በልተናል፤ ጠጥተናል፤ በአደባባያችንም አስተምረሃል ትላላችሁ።

27 “እርሱም፣ እላችኋለሁ፤ ‘ማን እንደሆናችሁና ከየት እንደመጣችሁ አላውቅም፤ እናንት ዐመፀኞች ሁሉ ከእኔ ራቁ’ ይላል።

28 “አብርሃምን፣ ይስሐቅንና ያዕቆብን፣ ነቢያትንም ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ስታዩ፣ እናንተ ግን ወደ ውጭ ተጥላችሁ ስትቀሩ በዚያን ጊዜ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።