26 ደግሞም የጌታን መሲሕ ሳያይ እንደማይሞት በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ነበር፤
27 እርሱም በዚህ ጊዜ በመንፈስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ የልጁም ወላጆች በሕጉ ልማድ መሠረት ተገቢውን ሊፈጽሙለት ሕፃኑን ኢየሱስን ይዘው በገቡ ጊዜ፣
28 ስምዖን ተቀብሎ ዐቀፈው፤ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እንዲህ አለ፤
29 “ጌታ ሆይ፤ ቃል በገባኸው መሠረት፣አሁን ባሪያህን በሰላም አሰናብተው፤
30 ዐይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን፣
31 ማዳንህን አይተዋልና።
32 ይህም ለአሕዛብ መገለጥን የሚሰጥ ብርሃን፣ለሕዝብህ ለእስራኤልም ክብር ነው።”