32 በድኑ በማንኛውም ዕቃ ላይ ቢወድቅ ያ ዕቃ ከዕንጨት፣ ከጨርቅ፣ ከቈዳ ወይም ከበርኖስ የተሠራ ቢሆን ርኩስ ይሆናል፤ በውሃ ውስጥ ይደረግ፤ ሆኖም ርኩስ ነው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
33 በድኑም በሸክላ ዕቃ ውስጥ ቢወድቅ፣ በውስጡ ያለ ነገር ሁሉ ርኩስ ስለሚሆን ዕቃውን ስበሩት።
34 ማንኛውም ምግብ እንዲህ ካለው ዕቃ ውሃ ቢፈስበት ይረክሳል፤ ከዚህ ዕቃ የሚጠጣውም ነገር ሁሉ ርኵስ ነው፤
35 ከበድናቸው አንዱ የወደቀበት ነገር ሁሉ ይረክሳል፤ ምድጃም ይሁን ማሰሮ ይሰበር፤ ርኩሳን ናቸው፤ እናንተም ተጸየፏቸው።
36 ነገር ግን ምንጭ ወይም የውሃ ማጠራቀሚያ ጒድጓድ ንጹሕ እንደሆነ ይቈያል፤ ሆኖም በድኑን የነካ ይረክሳል።
37 በሚዘራ ዘር ላይ በድን ቢወድቅ ዘሩ ንጹሕ እንደሆነ ይቆያል።
38 ነገር ግን በዘሩ ላይ ውሃ ከፈሰሰበት በኋላ በድን ቢወድቅበት ዘሩ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።