1 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ማንኛውም ሰው ከዘመዶቹ መካከል ስለ ሞተው ሰው ራሱን አያርክስ፤
2 ነገር ግን የቅርብ ዘመዶቹ ስለሆኑት እናቱ፣ አባቱ፣ ወንድ ልጁ፣ ሴት ልጁ፣ ወይም ወንድሙ፣
3 እንዲሁም ባለማግባቷ ከእርሱ ጋር ስለ ምትኖር እኅቱ ራሱን ሊያረክስ ይችላል።
4 ከእርሱ ጋር በጋብቻ ለሚዛመዱት ግን ራሱን አያርክስ።