1 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፤
2 “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፤ ‘ማንም ሰው ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸውም አንዱን ተላልፎ ቢገኝ፣
3 “ ‘የተቀባውም ካህን በሕዝቡ ላይ በደል የሚያስከትል ኀጢአት ቢሠራ፣ ስለ ሠራው ኀጢአት እንከን የሌለበት አንድ ወይፈን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ።
4 ወይፈኑን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያቅርብ፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጫን፤ በእግዚአብሔርም (ያህዌ) ፊት ይረደው።