ዘሌዋውያን 7:10-16 NASV

10 ማናቸውም በዘይት የተለወሰ ወይም ደረቅ የእህል ቊርባን ለአሮን ልጆች ሁሉ እኩል ይሰጥ።

11 “ ‘አንድ ሰው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የኅብረት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ሊከተለው የሚገባው ሥርዐት ይህ ነው፦

12 “ ‘መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ለምስጋና መግለጫ ከሆነ፣ ከምስጋና መሥዋዕቱ ጋር ያለ እርሾ የተጋገረና በዘይት የተለወሰ ኅብስት እርሾ ሳይገባበት በሥቡ ተጋግሮ ዘይት የተቀባ ቂጣ በሚገባ ታሽቶ በዘይት የተለወሰም የላመ ዱቄት ኅብስት አብሮ ያቅርብ።

13 ለምስጋና ከሚሆነው የኅብረት መሥዋዕት ጋር በእርሾ የተጋገረ ኅብስት ያቅርብ።

14 ከእያንዳንዱም ዐይነት አንዳንድ አንሥቶ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተለየ ቊርባን በማድረግ ያቅርብ፤ ይህም የኅብረት መሥዋዕቱን ደም ለሚረጨው ካህን ይሰጥ።

15 ለምስጋና የሚሆነው የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ፣ በቀረበበት ዕለት ይበላ እንጂ አንዳች አይደር።

16 “ ‘መሥዋዕቱ ስእለት በመፈጸሙ ወይም በበጎ ፈቃድ የሚቀርብ ከሆነ፣ በቀረበበት ዕለት ይበላ፤ የተረፈውም ሁሉ በማግስቱ ይበላ።