30 ከእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ደግሞ ከሰውም ይሁን ከቀንድ ከብት፣ ከአህያ፣ ከበግ፣ ከፍየል ወይም ከሌሎች እንስሳት ከየአምሳው አንዳንድ መርጠህ፣ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ማደሪያ ድንኳን በኀላፊነት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ስጣቸው።”
31 ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።
32 ወታደሮቹ ማርከው ከወሰዱለት ምርኮ ውስጥ የቀረው ይህ ነበር፤ ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ በግ፣
33 ሰባ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብት፣
34 ሥልሳ አንድ ሺህ አህያ
35 ወንድ ያላወቁ ሠላሳ ሁለት ሺህ ሴቶች።
36 በጦርነቱ ላይ የነበሩት ወታደሮች እኩሌታ ድርሻ ይህ ነበር፤ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ በግ፤