14 ዳዊትም፣ “ታዲያ እግዚአብሔር የቀባውን ለማጥፋት እጅህን ስታነሣ እንዴት አልፈራህም?” ሲል ጠየቀው።
15 ዳዊትም ከጒልማሶቹ አንዱን ጠርቶ፣ “በል ቅረብና ውደቅበት” አለው። እርሱም መታው፤ ሞተም።
16 ዳዊትም፣ “እግዚአብሔር የቀባውን ገድያለሁ’ ስትል የገዛ አፍህ መስክሮብሃልና፣ ደምህ በራስህ ላይ ይሁን” አለው።
17 ዳዊትም በሳኦልና በልጁ በዮናታን ሞት ምክንያት ይህን የሐዘን እንጒርጒሮ እየተቀኘ አለቀሰ፤
18 እንዲሁም የቀስት እንጒርጒሮ የተባለውን ለይሁዳ ሕዝብ እንዲያስተምሩ አዘዘ፤ ይህም በያሻር መጽሐፍ ተጽፎአል።
19 “እስራኤል ሆይ፤ ክብርህ በኰረብቶችህ ላይ ተወግቶ ሞቶአል፤ኀያላኑ እንዴት እንደዚህ ይውደቁ!
20 “ይህን በጌት አትናገሩ፤በአስቀሎናም መንገዶች አታውጁት፤የፍልስጥኤም ቈነጃጅት አይደሰቱ፤ያልተገረዙት ሴቶች ልጆች እልል አይበሉ።