21 ደግሞም አንድ ግዙፍ ግብፃዊ ገድሎአል፤ ግብፃዊው በእጁ ጦር የያዘ ቢሆንም፣ በናያስ ግን ሊገጥመው በትር ይዞ ወደ እርሱ ሄደ፤ ከግብፃዊውም እጅ ጦሩን በመንጠቅ በገዛ ጦሩ ገደለው።
22 የዮዳሄ ልጅ የበናያስ ጀግንነት እንደዚህ ያለ ነበረ፤ እርሱም እንደ ሦስቱ ኀያላን ሁሉ ዝናን ያተረፈ ሲሆን፣
23 ከሠላሳዎቹ ሁሉ በላይ የከበረ ሰው ነበረ፤ ነገር ግን ከሦስቱ እንደ አንዱ አልነበረም። ዳዊትም የክብር ዘበኞቹ አለቃ አድርጎ ሾመው።
24 ከሠላሳዎቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙ ባቸዋል፤የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣
25 አሮዳዊው ሣማ፣አሮዳዊው ኤሊቃ፣
26 ፈሊጣዊው ሴሌስ፣የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ፣
27 ዓናቶታዊው አቢዔዜር፤ኩሳታዊው ምቡናይ፣