22 ኦርናም ዳዊትን እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ ጌታዬ ደስ ያለውን ወስዶ መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎች አሉ፤ ለሚነደውም ዕንጨት፣ የመውቂያው ዕቃና የበሬ ቀንበር አለ።
23 ንጉሥ ሆይ፣ ይህን ሁሉ ኦርና ለንጉሡ ይሰጣል።” እንዲሁም ኦርና፣ “እግዚአብሔር አምላክህ ይቀበልህ” አለው።
24 ንጉሡ ግን ኦርናን፣ “እንዲህማ አይሆንም፤ ዋጋውን ላንተ መክፈል አለብኝ፤ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም” አለው።ስለዚህም ዳዊት ዐውድማውንና በሬዎቹን በአምሳ ሰቅል ብር ገዛ፤
25 በዚያም ዳዊት ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ። ከዚያም እግዚአብሔር ስለ ምድሪቱ የቀረበውን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የመጣውም ቸነፈር ቆመ።