መሳፍንት 5:11-17 NASV

11 የዝማሬ ድምፅ ስሙ።ይህም የእግዚአብሔር የጽድቅ ሥራ፣ጦረኞቹም በእስራኤል ያደረጉትን ያስታውሳል።“ከዚያም የእግዚአብሔር ሕዝቦች፣ወደ ከተማዪቱ በሮች ወረዱ፤

12 ‘ዲቦራ ሆይ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ንቂ፤ ንቂ፤ ቅኔም ተቀኚ፤የአቢኒኤል ልጅ ባራቅ ሆይ፤ ተነሣ፤ምርኮኞችህንም ማርከህ ውሰድ’ አሉ።

13 የቀሩትም ሰዎች፣ወደ መኳንንቱ ወረዱ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ እንደ ኀያል ጦረኛ ወደ እኔ መጣ።

14 መሠረታቸው ከአማሌቅ የሆነ አንዳንዶችከኤፍሬም መጡ፤ ብንያም አንተን ከተከተሉ ሰዎች ጋር ነበር፤የጦር አዛዥች ከማኪር፣የሥልጣን በትር የያዙም ከዛብሎን ወረዱ።

15 የይሳኮር መሳፍንት ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤ይሳኮርም ራሱ ወደ ሸለቆው ከኋላውበመከተል፣ ከባርቅ ጋር ነበረ።በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብምርምር ነበር።

16 በበጎች ጒረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ?መንጎችን የሚጠራውን ፉጨት ለመስማት ነውን?በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብምርምር ነበር።

17 ገለዓድ ከዮርዳኖስ ማዶ ተቀመጠ፤ዳን ለምን በመርከብ ውስጥ ዘገየ?አሴር በጠረፍ ቀረ፤በባሕሩ ዳርቻም ተቀመጠ።