መሳፍንት 5:9-15 NASV

9 ልቤ ከእስራኤል መሳፍንት፣ፈቃደኞችም ከሆኑ ሰዎች ጋር ነው፤እግዚአብሔር ይመስገን።

10 “እናንት በነጫጭ አህዮች የምትጋልቡ፣በባለ ግላስ ኮርቻ ላይ የምትቀመጡ፣በመንገድ ላይ የምትጓዙ፣በውሃ ምንጮች ዙሪያ ያለውን፣

11 የዝማሬ ድምፅ ስሙ።ይህም የእግዚአብሔር የጽድቅ ሥራ፣ጦረኞቹም በእስራኤል ያደረጉትን ያስታውሳል።“ከዚያም የእግዚአብሔር ሕዝቦች፣ወደ ከተማዪቱ በሮች ወረዱ፤

12 ‘ዲቦራ ሆይ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ንቂ፤ ንቂ፤ ቅኔም ተቀኚ፤የአቢኒኤል ልጅ ባራቅ ሆይ፤ ተነሣ፤ምርኮኞችህንም ማርከህ ውሰድ’ አሉ።

13 የቀሩትም ሰዎች፣ወደ መኳንንቱ ወረዱ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ እንደ ኀያል ጦረኛ ወደ እኔ መጣ።

14 መሠረታቸው ከአማሌቅ የሆነ አንዳንዶችከኤፍሬም መጡ፤ ብንያም አንተን ከተከተሉ ሰዎች ጋር ነበር፤የጦር አዛዥች ከማኪር፣የሥልጣን በትር የያዙም ከዛብሎን ወረዱ።

15 የይሳኮር መሳፍንት ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤ይሳኮርም ራሱ ወደ ሸለቆው ከኋላውበመከተል፣ ከባርቅ ጋር ነበረ።በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብምርምር ነበር።